Different Forms to Dowenload

                              ፓስፖርት ለማመልከት
ፓስፖርት ማውጣት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል ወደ ውጭ ሲወጡ የተጠቀሙበትን ኦሪጅናል ፓስፖርት ወይም ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ካልቻሉ በልደት የምስክር ወረቀት ብቻ ልናስተናግድ የማንችል መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ ይህ ወላጆቻቸው ኢትዮጵያዊ ሆነው በውጪ ሀገር የተወለዱ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስፖርት ሚጠይቁ ህፃናትን አይመለከትም፡፡

1.1 አገልግሎቱ ያለቀበት ማንዋል   ፓስፖርት ለመቀየር  መሟላት የሚገባቸውመስፈርቶች

·         ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ኦሪጅናል ፓስፖርት ማቅረብ

·         የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽበሁለት ኮፒ መሙላት

·         ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለትኮፒ ማቅረብ

·         ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ

·         የቀኝ እና የግራ የቀኝ አመልካች ጣቶች በተዘጋጀው ፎርም ላይ የጣት አሻራ ማቅረብ::

·         4 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም ከነአያት የተፃፈበት)

·         የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

·         በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎበት ህጋዊነቱ የተረጋገጠ መሆን አለበት::

·         የአገልግሎት ክፍያ€54.00 መፈፀም

·         በፓሪስና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማንዋል ፓስፖርት ያላቸውአገልግሎት ጠያቂዎች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ በመያዝ አሻራ በኤምባሲው ቆንስላክፍል ይሰጣሉ

1.2 አገልግሎቱ ያለቀበት ኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት ለመቀየር  መሟላት የሚገባቸውመስፈርቶች

·         ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገውን ኦሪጅናል ፓስፖርት ማቅረብ

·         የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽበሁለት ኮፒ መሙላት

·         ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለትኮፒ ማቅረብ

·         ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ

·         3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለ)ማቅረብ

·         የአገልግሎት ክፍያ€54.00  መፈፀም

·         እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀድሞ ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዱሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

·         ‘የፓስፖርት አገልግሎቱ የሚሰጠው በፖስታቤት በኩል ስለሆነ አድራሻዎ የተፃፈበት መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ’

·         ፓስፖርታቸው በአስቸኳይ እንዲታደስላቸው የሚፈልጉ ተገልጋዮች በራሳቸው ወጭ በአለም አቀፍ የፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች መላክ የሚችሉ ሲሆን ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ግን ወደ ኢምባሲው የሚመጣው በዲፕሎማቲክ ፓውች ብቻ ነው

1.3 ኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት በጠፋ ምትክ ሲጠየቅ

·         የጠፋው ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ ሲቀርብ ወይም የጠፋው ፓስፖርት ቁጥር ሲታወቅ

·         ፓስፖርቱ ስለመጥፋቱ በፖሊስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ አያይዘው ሲያቀርቡ

·         3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም ከነአያት የተፃፈበት)

·         ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ

·         2 የፓስፖርት መጠየቂያ ማመልከቻ ቅፅ ሞልተው ሲያቀርቡ/ ሲልኩ

·         የፓስፖርት አገልግሎቱ የሚሰጠው በፖስታቤት በኩል ስለሆነ አድራሻዎ የተፃፈበት መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ

·         ፓስፖርታቸው በአስቸኳይ እንዲታደስላቸው የሚፈልጉ ተገልጋዮች በራሳቸው ወጭ በአለም አቀፍ የፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች መላክ የሚችሉ ሲሆን ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ግን ወደ ኢምባሲው የሚመጣው በዲፕሎማቲክ ፓውች ብቻ ነው

·         አገልግሎትክፍያ:-

o    ለመጀመሪያ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 50 %  (81.00 €)

o    ለሁለተኛ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 100 % (108 €)

o    ለሶስተኛ ጊዜ ምትክ በ5 አመት ጊዜ ውስጥ ጥያቄ ከቀረበ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 200 % (162 €)

o    በፓሪስና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማንዋል ፓስፖርት የጠፋባቸው አገልግሎትጠያቂዎችበቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ በመያዝ አሻራበኤምባሲውቆንስላክፍልይሰጣሉ

o    የፓስፖርትአገልግሎቱየሚሰጠው በፖስታቤት በኩልስለሆነ አድራሻዎየተፃፈበትመመለሻፖስታከነቴምብሩአብሮመላክ

1.4 በጠፋ  ማንዋል ፓስፓርት ምትክ  ሲጠየቅ መሟላትየሚገባቸውመስፈርቶች

·         የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትንማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ  ፎቶ ኮፒ ማቅረብ

·         የፓስፓርቱን ፎቶኮፒ ማግኘት ካለተቻለ የቤተሰብ ሙሉ አድራሻ እና ቤተሰቦች ከሚኖሩበት ቀበሌ ኢትዮጵያዊነትዎን የሚያረጋግጥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ካርድ ማቅረብ

·         ፓስፖርቱ ለመጥፋቱ በፖሊስ የተመዘገቡበት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ

·         የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽበሁለት ኮፒ መሙላት

·         4 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም ከነአያት የተፃፈበት) ተያይዞ ሲቀርብ

·         ያሉበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ

·         የቀኝ እና የግራ አመልካች ጣቶች በተዘጋጀው ፎርም ላይ መስጠት/መላክ   የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች  አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

·         በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎ  የተረጋገጥ  መሆን አለበት

·         በፓሪስና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማንዋል ፓስፖርት የጠፋባቸው አገልግሎት ጠያቂዎች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ በመያዝ አሻራ በኤምባሲው ቆንስላክፍል ይሰጣሉ

·         ፓስፖርታቸው በአስቸኳይ እንዲታደስላቸው የሚፈልጉ ተገልጋዮች በራሳቸው ወጭ በአለም አቀፍ የፖስታ አገልግሎት ድርጅቶች መላክ የሚችሉ ሲሆን ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ግን ወደ ኢምባሲው የሚመጣው በዲፕሎማቲክ ፓውች ብቻ ነው

·         የአገልግሎት ክፍያ :-

o    ለመጀመሪያ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 50 % (81.00 €)

o    ለሁለተኛ ጊዜ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 100 % (104 €)

o    ለሶስተኛ ጊዜ ምትክ በ5 አመት ጊዜ ውስጥ ጥያቄ ከቀረበ ከመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 200 % (162 €)

ለተለያዩ የፓስፖርት አይነቶች ያሉትን የክፍያ ተመኖች ለማወቅ እዚህ ይጫኑ፡፡ የተዘረዘሩት ዋጋዎች በ አሜሪካን ዶላር ሲሆን ትክክለኛ የዩሮ መጠኑን ለማወቅ ቆንስላ ክፍል በመደወል መጠየቅ ይቻላል ፡፡

ማሳሰቢያ

·         ለኤምባሲው የቆንስላ ክፍል የሚቀርብ አገልግሎት በፖስታ ቤት ከሆነ የባለ ጉዳዩን ሙሉ አድራሻ   የተጻፈበት የአደራ መልእክት (ሬኮማንዴ )መመለሻ  የ6  ዩሮ  ቴምብር አብሮ/ለጥፎ  መላክ::

·         በስፔይን እና ፖርቱጋልየሚኖሩ አገልግሎት ፈላጊዎች ፓስፓርታቸውን ሲልኩ ለመመለሻ የሚሆን በቁጥር 9 ኢንተርናሽናል ኩፖንና ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

·         ለልጆቻቸው ፓስፖርት የሚይቁ ወላጆች በጽሁፍ ማመልከቻ ፣  የወላጅ ፓሰፖርት ና የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ እንዲሁም የልጆቹ የልደት ካርድ ተያይዞ መቅረብ አለበት

·         በትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎች ፓስፖርት ለማሳደሰም ሆነ አዲስ ሲያወጡ የሚማሩበትን ተቋም መተወቂያ አያይዘው ሲያቀርቡ የግኛማሽ ክፍያ ተጠቃሚይሆናሉ

የሊሴ ፓሴ አገልግሎት
የይለፍ (ሌሴ ፓሴ) ሰነድ ለመጠቅ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
·         አመልካች በአካል መቅረብ

·         ፓስፖርት ወይንም ሌላ የመጓጓዛ ሰነድ የሌላቸውና ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ወይም የቤተሰብን ሙሉ አድራሻ ማሳወቅ

·         የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽ(የይለፍ ሰነድ የሚለው ላይ ምልክት በማድረግ) ሁለት ኮፒ መሙላት

·         ሁለት የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለ)ማቅረብ

·         የአገልግሎት ክፍያ 42.50€ መፈፀም

·         አመልካቹ በቅድሚያ በሰልክ ቀጠሮ አስይዘው በአካል ሲቀርቡ

ከወንጀል ነጻ መሆንን ለማረጋገጥ አሻራ መቀበልና መላክ አገልግሎት

*ጠቃሚ ማስታወሻ – ከወንጀል ነጻ መሆንን ለማረጋገጥ አሻራ ለመስጠት ወደ ኤምባሲያችን ከመምጣትዎ በፊት በ 01 47 83 27 42 ወይም 01 47 83 26 35 በመደወል ቀጠሮ መያዝ እንደሚያስፈልግ እናሳስባለን

·         አገልግሎት ጠያቂው በአካል ቀርቦ አሻራ ይሰጣል፣

·         በአካል መቅርብ የማይችሉ ተገልጋዮች የአሻራ ናሙና መቀበያ ቅጹን ከሚሲዮኑ ዌብ ሳይት ፕሪንት በማድረግና በአካባቢይቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም Nottary Office ቀርቦ አሻራ በመስጠት በሚኖሩበት አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጦ ወደ ኤምባሲው በፖስታ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡(ቅፁን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ)

·         በፖስታ ቤት በመላክ አገልግሎት የምትጠይቁ ባለጉዳዮች  የመላኪያውም ሆነ የመመለሻ ፖስታውን ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘትበተገልጋዮች መሟላትየሚገባቸውመስፈርቶች

·         አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይንም የትውልደ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ፎቶ ኮፒ

·         በጀርባው ላይ ሙሉ ስም የተፃፈበት ሁለት የፓስፖርት ልክ ፎቶ ግራፍ  ማቅረብ/መላክ (ፎቶግራፉ  3X4 መጠን ያለው ሆኖ ሁለት ጆሮዎችን ፊት ለፊት የሚያሳይና መደቡ ነጭ መሆን ይኖርበታል፡፡

·         ጉዳዩን በአገር ቤት ተከታትሎ ለሚያስፈፀም  ሰው የተሰጠ የውክልና   ሰነድ፣ (ሞዴሉን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ)

የአገልግሎት ክፍያ

·          ለኢትዮጵያዊያን እና ለትውልድ ኢትዮጵያውያን ሃምሳ ሰባት (57) ዩሮ፣

·          ለውጭ ዜጎች ሰማንያ ሰባት (87 ) ዩሮ ፣

·         አገልግሎቱን በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው፡፡ አገልግሎቱን በፖስታ ቤት በኩል ልከው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበትና  Tracking Number ያለው መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ የሚገባ ሲሆን ክፍያውን ለኤምባሲው የተፃፈ፡-

·         የክፍያ ትዕዛዝ  /MONDANT CASH/ ወይም

·         ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ በመላክ መክፈል ያስፈልጋል፡፡

የድጋፍ ደብዳቤዎች

ሀ/በፈረንሳይ እና ኤምባሲው በሚሸፍነው ሀገራት ነዋሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ
·         አገልግሎቱ የፀና  ፓስፖርት፤

·         የመኖሪያ ፍቃድ ኮፒ፤

·         በአድራሻቸው የተላከ የቤት ኪራይ፤የስልክ መክፈያ፤ወይም ሌላ የቋሚ ነዋሪነት ማስረጃ፤

·         ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ለ/በፈረንሳይ ወስጥ በሕይወት የሚኖሩ መሆኑን የሚያረጋግጥ  ድጋፍ ደብዳቤ

·         የመኖሪያ ፍቃድ ኮፒ

·         አገልግሎቱን በግንባር ቀርቦና ፈርሞ መጠየቅ፤

·         ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ሐ/ኢትዮጵያውያን የፈረንሳይ ወይም የሌላ ሀገር  ዜግነት ያልወሰዱ  መሆኑን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ

·         አገልግሎቱ የፀና  ፓስፖርት፤

·         አገልግሎቱን በጽሁፍ መጠየቅ

·         የመኖሪያ ፍቃድ ኮፒ፤

·         ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

መ/በኢትዮጵያ ባህል መሰረት የልጅ ሁለተኛ ስም የአባቱ የመጀመሪያ ስም መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ፤

·         አገልግሎቱ የፀና ኢትዮጵያ ፓስፖርት፤

·         የመኖሪያ ፍቃድ ኮፒ/የፓስፖርት ኮፒ፤

·         ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ሠ/የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን  የሚያረጋግጥ የግጋፍ ደብዳቤ፤

·         አገልግሎቱ የፀና ኢትዮጵያ ፓስፖርት፤

·         የመኖሪያ ፍቃድ ኮፒ/የፓስፖርት ኮፒ

·         ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ረ/ በፈረንሳይ ህይወቱ ያለፈ ዜጋ    1.ወደ ኢትዮጵያ አሰክሬኑ እንዲገባ የሚጠይቅ ደብዳቤ   2.የሞት ማስረጃውን ማረጋገጥ

·         የሆስፒታል የሞት ዲኪላሬሽን/ፖሊስ ማስረጃ

·         በሀገር ቤት የሚገኙ የሟች ቤተሰብ ሙሉ ስምና አድራሻ

·         የሟች የመኖሪያ ፍቃድ ኮፒ

ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

                                  የቪዛ አገልግሎት
ቪዛን በተመለከተ ጠቃሚ መረጃዎች

·       የቪዛ መጠየቂያ ማመልከቻ የሚገባው ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ 3ሰአት – 6ሰአት ከ45  ብቻ ሲሆን
ቪዛዎትን የመውሰጂያ ሰአት ደግሞ ከሰኞ እስከ አርብ ከሰአት በኋላ ከ9ሰአት እስከ 10ሰአት ከ45 ብቻ ነው፡፡

·         ቪዛ የሚጸናው ከተጠሰጠበቀት ቀን ጀምሮ ነው ፡፡ ሰለዚሆነም የቪዛ ማመልከቻዎን በመላላክ (በፖስታ) የሚጠይቁ ከሆነ በቂ ጊዜ እንዲኖሮት የ 3 ወር ቪዛ እንዲጠይቁ ይመከራል፡፡ የፈረንሳይ ፣ የስፔይን እና የፓርቹጋል ፓስፖርት ያላቸው አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ  የቱሪስት ቪዛ  መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

·         የትውልድ ኤርትራውያን የቪዛ ጠያቂዎች በአካል ኤምባሲያችን ድረስ በመምጣት የቪዛ መጠየቂያ ፎርም መውሰድ ይችላሉ ፡፡

ዲፕሎማቲክ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

·         ቀኑ ያላለፈበት ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ

·         የቪዛ መጠየቂያ ፎርም ተሞልቶ ከ1 ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ

·         ከጠያቂው አገር ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ወይም ከሚሰሩበት አለም አቀፍ ድርጅት ኖት ቨርባል ተያይዞ ሲቀርብ

·         የዲፕሎማት ቪዛ የተሰጠው ዲፕሎማት ቤተሰብ አባላትም የዲፕሎማቲክ ቪዛ ይሰጣቸዋል

·         ዲፕሎማቲክ ቪዛ ከክፍያ ነፃ ነው

·         ፎቶ ግራፍ ያለበት የፓስፖርቱ ገፅኮፒ ተያይዞ ሲላክ

·         የዲፕሎማቲክ ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

ሰርቪስ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

·         ቀኑ ያላለፈበት ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ

·         የቪዛ መጠየቂያ ፎርም ተሞልቶ ከ1 ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ

·         ከጠያቂው አገር ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ወይም ከሚሰሩበት አለም አቀፍ ድርጅት ኖት ቨርባል ተያይዞ ሲቀርብ

·         የሰርቪስ  ቪዛ የተሰጠው ግለሰብ ቤተሰብ አባላትም የሰርቪስ  ቪዛ ይሰጣቸዋል

·         የሰርቪስ ቪዛ ከክፍያ ነፃ ነው

·         ፎቶ ግራፍ ያለበትየፓስፖርቱ ገፅኮፒ ተያይዞ ሲላክ

·         የሰርቪስ ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

የቱሪስት ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

·         የቪዛ መጠየቂያ ፎርም ከ1 ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ

·         ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ

·         የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ

·         በፈረንሳይ በስፔንና ፖርቱጋል  ኗሪ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች  የሚኖሩበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ  አያይዘው ሲያቀርቡ

·         ፎቶ ግራፍ ያለበት የፓስፖርቱ ገፅ ኮፒ ተያይዞ ሲላክ

·         የቱሪስት ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

ለትውልድ ኤርትራውያን 

·         የትውልድ ኤርትራውያን የቪዛ ጠያቂዎች በአካል ኤምባሲያችን ድረስ በመምጣት የቪዛ መጠየቂያ ፎርም መውሰድ ይችላሉ ፡፡

የቱሪስት ቪዛ የዋጋ ዝርዝር

ፈረንሳይ ሲጠየቅ
አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲጠየቅ
አንድ ጊዜ መግቢያ
1 ወር
36€
ለአንድ ጊዜ መግቢያ
1 ወር
45€
3 ወር
54€
3 ወር
63€
ለብዙ ጊዜ መግቢያ
3 ወር
63€
ለብዙ ጊዜ መግቢያ
3 ወር
72€
የትራንዚት ቪዛ የዋጋ ዝርዝር

ለ 12 ሰአት
21.50€
ለ 24 ሰአት
36.00€
ለ 48 ሰአት
45.00€
ለ 72 ሰአት
54.00€ 

የሥራ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

·         የሥራ  ቪዛ በአመልካቹ ወይም በወኪሉ አማካኝነት የመጠቂያ ፎርም ተሞልቶ  ከአንድ ጉርድ  ፎቶ ግራፍ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ

·         አመልካቹ ወደ ኢትዮጵያ ለስራ የሚሄዱበትን ምክንያት ሊያስረዳ የሚችል  ደብዳቤ ማቅረብ ሲችሉ

·         አመልካቹን ኢትዮጵያ የሚጋብዘው ድርጅት አዲስ አበባ ኢሚግሬሽን ቀርቦ ለአመልካች የስራ ቪዛ ፈቃድ ጠይቆ ሲያገኝ

·         ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ

·         የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ

·         በፈረንሳይ በስፔንና ፖርቱጋል  ኗሪ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች  የሚኖሩበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ  አያይዘው ሲያቀርቡ

·         ፎቶ ግራፍ ያለበት የፓስፖርቱ ገፅኮፒ ተያይዞ ሲላክ

·         የስራ ቪዛ የሚሰጠው በፖስታ አገልግሎት ብቻ ነው

የስራ ቪዛ የዋጋ ዝርዝር

የቪዛ አይነት
የቪዛው መጠሪያ 
            የቪዛው ዋጋ
ለአንድ ጊዜእስከ 1 ወር
ለለአንድ ጊዜእስከ 3 ወር
ለ ብዙ ጊዜእስከ 3 ወር
ለኢንቨስትመንት / ለንግድ ስራ/
I-V
          27.00€

   36.00 €
ለተለያዩ መንግስታዊ ለሆኑ ስራዎች
G-I-V
          18.00€

  72.00 €
ለውጭ ባለሀብት ተቀጣሪ
W-V
          36.00€
 54.00€
  72.00 €
ለመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጣሪ
G-V
          27.00€
36.00€
54.00€
ለNGO
N-V
          54.00€


ለ አህጉራዊና አለምአቀፍ ድርጅት ተቀጣሪ
R-I
          45.00€
63.00€
81.00€
ለአጭር ስብሰባ ፣ለወርክ ሾፕ፣ለ አውደ ጥናት
C-V
          27.00€


ለሚዲያ ጋዜጠኞች
J-V
          36.00€


ለግል ድርጅት ተቀጣሪ
P-E
          27.00€
45.00€
72.00€ 

የትራንዚት ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

·         ቪዛ ጠያቂው ኢትዮጵያን አቋርጦ ለማለፍ በራሱ ወይም በወኪሉ አማካኝነት ጥያቄ ሲያቀርብ 

·         ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ

·         የደርሶ መመለሻ  የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ

·         በፈረንሳይ በስፔንና ፖርቱጋል  ኗሪ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች  የሚኖሩበትን አገር የመኖሪያ ፈቃድ  አያይዘው ሲያቀርቡ

የትራንዚት ቪዛ የዋጋ ዝርዝር

ለ 12 ሰአት
21.50€
ለ 24 ሰአት
36.00€
ለ 48 ሰአት
45.00€
ለ 72 ሰአት
54.00€
ለኤርትራዊያን የቱሪስት ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

·         ቋሚ መኖሪያቸው በኤርትራ ውስጥ ለሆኑ ኤርትራዊያን ቅፅ አንድ እንዲሁም ከኤርትራ ውጭ ለሚኖሩ ትውልድ ኤርትራዊያን ለሆኑ አመልካቾች ቅፅ 2 ተሞልቶ ሲቀርብ

·         በተሞላው ቅፅ መሰረት  ተጨማሪ ማጣራት አድርጎ  ወደ በላይ አካል ከተላከ በኋላ ቪዛው ሲፈቀድ

·         የደርሶ መመለሻ  የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ

·         የቱሪስት ቪዛ አገልግሎት ለመጠየቅ በቅድሚያ ስልክ ደውለው ቀጠሮ ሲያሲዙ ብቻ ይስተናገዳሉ

ለኤርትራዊያን የሥራ ቪዛ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

·         የቪዛ አገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ 1 በአግባቡ ተሞልቶ ሲቀርብ፣

·         የደርሶ መመለሻ  የአውሮፕላን ቲኬት አያይዘው ሲያቀርቡ፣

·         ቀኑ ያላለፈበት  ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፀና የጉዞ ሰነድ ሲቀርብ፣

·         አመልካቹን ኢትዮጵያ የሚጋብዘው ድርጅት አዲስ አበባ ኢሚግሬሽን ቀርቦ ለአመልካች የስራ ቪዛ ፈቃድ ጠይቆ ሲያገኝ

·         ለኢንቨስትመንት ስራ የሚሄዱ ከሆነ መኢንቨስትመንት መሄዳቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ  አያይዘው ሲያቀርቡ፣

·         ለስራ ተቀጥረው የሚሄዱ ከሆነ የቀጣሪ ድርጅቱ ዝርዝር መረጃና ይድጋፍ ደብዳቤ እንዲሁም፣

የሚሲዮኑ የውሳኔ ሀሳብ ታክሎበት የበላይ አካል በሚወስነው መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፣

የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት
ከኢትዮጵያ ውጭ የመነጨ ሰነድ ለማረጋገጥ፣
·         ሰነዱ በመነጨበት አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል፣

·         የአገልግሎት ክፍያ :-

o    ለኢትዮጵያዊያን እና ለትውልድ ኢትዮጵያዊያን ሃምሳ ሰባት(57€ )

o    ለውጭ ዜጎች ሰማንያ ሰባት (87)

o    በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው፡፡

o    አገልግሎቱን በፖስታ ቤት በኩል ልከው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበትና  Tracking Number ያለው መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ይገባል፡፡

o    በፖስታ ሲላክ ክፍያው ለኢትዮጵያ ለኤምባሲ (AMBASSADE D’ETHIOPIE PARIS) የተፃፈ፡-
የክፍያ ትዕዛዝ /MANDANT CASH/ ወይም   ካሽየር ቼክ /Cashier Check/  በመላክ መክፈል ያስፈልጋል፡፡

ከኢትዮጵያ የመነጨ ሰነድ ማረጋገጥ

·         ሰነዱ በኢትዩጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል፣

·         የአገልግሎት ክፍያ

o    ለኢትዮጵያዊያን እና ለትውልድ ኢትዮጵያዊያን ሃምሳ ሰባት (57) ዩሮ

o    ለውጭ ዜጎች ሰማንያ ሰባት (87) ዩሮ

o    በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው፡፡

o    አገልግሎቱን በፖስታ ቤት በኩል ልከው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበትና  Tracking Number ያለው መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ይገባል፡፡

በፖስታ ሲላክ ክፍያው ለኢትዮጵያ ለኤምባሲው በተፃፈ፡-
የክፍያ ትዕዛዝ /MONDANT CASH/ ወይም
ካሽየር ቼክ /Cashier Check/  በመላክ መክፈል ይቻላል

             የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ አገልግሎት

1 የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጠው ያመለከተ የኢትዮጵያ ተወላጅ  የሆነ የውጭ አገር ዜጋ

·         መታወቂያን ለማግኘት ዜግነት ከወሰደበት አገር የተሰጠው አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት ማቅረብ

·         የአመልካቹ አግባብ ካለው አካል የተረጋገጠ የልደት ምስክርወረቀት  ወረቀት ዋናውን ከሁለት ቅጂዎች  ወይም

·         የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት  ቅጂ ዋናውን ከሁለት ቅጂዎች ጋር ወይም

·         ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ኢትዮጵያዊያን ከሆኑ/ከነበሩ የስጋ (biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነተ ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ወይም

·         ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ  በኢትዮጵያዊያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ  ኢትዮጵያዊ አንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ወይም

·         ስልጣን ካለው ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰነድ ማስረጃ ወይም

·         ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨበጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም አያቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ

·         3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው  ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ

·         አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች  አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

·         በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ትውልድ  ኢትዮጵያውያን ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 5 በመጠቀም በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎበት ህጋዊነቱ የተረጋገጠ መሆን አለበት::

·         ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 1 በሁለት ኮፒ መሙላት

·         የአገልግሎት ክፍያ 200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም

·         አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁት አገልጋዮች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ለማውጣት የአገልግሎት የክፍያ ዝርዝር ለማወቅ እዚህ ይጫኑ

2. አካለ መጠን ላልደረሱ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጆች ስለሚሰጥ አገልግሎት

·         የልጁ/የልጅቷ ፓስፖርት ቢያንስ ለስድስት ወራት አገልግሎቱ የፀና ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር

·         የልጁን/የልጅቷን የተረጋገጠና ህጋዊ የልደት ምስክር ወቀት ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር

·         የወላጁ/የወላጇ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር

·         ልጁ/ልጅቷ ከማመልከቻ ቅፅ ጋር በማያያዝ ከ6ወር ወዲህ የተነሳው/የተነሳችው 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነ  ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው  ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ

·         ከላይ የተጠቀሱትን ካሟሉ በኋላ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አገልግሎት ክፍያውን 20 የአሜሪካን ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ፈፅሞ መታወቂያው እንዲሰጥለት በወላጅ ጥያቄው ሲቀርብ ሊሰጠው ይችላል

·         ዕድሜ 14 ዓመትና ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆችና 18 ዓመት ያልሞላቸው የጣት አሻራ መስጠት ይጠበቅባቸዋል

·         የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጆች እድሜያቸው ለአካለ መጠን ሲደርስ በራሳቸው ጠያቂነት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ  መስፈርትን ሲያሟሉ የተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጣቸው ይደረጋል

·         ማንዋልየትውልድኢትዮጵያ ለማደስወደኢምባሲውበአካልቀርበውለሚጠይቁተገልጋዮችበቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራበኤምባሲውበቆንስላክፍልይሰጣል

·         የአገልጎሎት ክፍያ፡-

o    ከ 18 አመት በታች ለሆኑ 20 የአሜሪካን ዶላር በእለቱ ዋጋ ወደ ይሮ ተቀይሮ

3. የኢትዮጵያ ተወላጅ የትዳር ጓደኛ ስለሚሰጥ የኢትዮጵያ ተወላጅነት     መታወቂያ

·         የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ያለው/ያላት የውጭ አገር ዜጋ ለትዳር ጓደኛው/ጓደኛዋ የአትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጥለት/ እንዲሰጥላት ከፈለገ/ች

·         መታወቂያውን ለማግኘት ዜግነት ከወሰደችበት/ ከወሰደበት አገር የተሰጣትን/የተሰጠውን አገልግሎቱ ቢያንስ ለስድስት ወር የፀና ፓስፖርት ዋናውንና ከሁለት ቅጅ ጋር

·         መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙበት የቃለ መሃላ ሰነድ ተያየዞ ሲቀርብና የጋብቻ ሰነዱ በእንግሊዝኛ ተተርጉሞና በፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ሲቀርብ

·         የትዳር ጓደኛው/ዋ  ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሳውን/የተነሳችውን 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነ  ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ

·         ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ  2 በሁለት ኮፒ መሙላት

·         የአገልግሎት ክፍያ 200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም

·         የእጅ አሻራ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 5 በመጠቀምስጠት፡

o     አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁ ተገልጋዮች  አሻራው በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

o    በፈረንሳይ ክ/ሀገራት በስፔንና በፖርቱጋል የሚኖሩ ትውልድ  ኢትዮጵያውያን በአካባቢው ፖሊስ ወይም ህጋዊ አካል ከተነሱ በኋላ ከጀርባው ማህተም ተደርጎበት ህጋዊነቱ የተረጋገጠ መሆን አለበት ::

o    አገልግሎትለማግኘትወደኢምባሲውበአካልቀርበውከመጠየቃቸው በፊትበቅድሚያ ቀጠሮ በስልክ አስይዘው አሻራበኤምባሲውበቆንስላክፍልይሰጣል

·         መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ ፀንቶ ስለመኖሩ በማስረጃ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡

·         የአገልግሎት ክፍያ ፡-

o    200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም

o    አገልግሎት ለማግኘት ወደኢምባሲው በአካል ቀርበው ከመጠየቃቸው በፊት በቅድሚያ ቀጠሮ በስልክ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

 4. የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ  እድሳት

·         ዜግነት ካገኘበት ሀገር የተሰጠውና ቢያንስ ለስድስት ወር አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር

·         ቀደም ሲል የተሰጠው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር

·         የአገልግሎት ክፍያ 200 አሜሪካን ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም፣እንዲሁም መታወቂያውን በወቅቱ ያላሳደሱ በየቀኑ የሚከፈለውን መቀጮ  መክፈላቸው ሲረጋገጥ

·         በጋብቻ ምክንያት  የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት ቃለ መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ

·         የትዳር ጓደኛው/ዋ  ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሳውን/የተነሳችውን 3 የፓስፖርት መጠን(3 x4cm )የሆነ  ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎችንና ፊትን ሙሉ ለሙሉ  የሚያሳይ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም  የተፃፈበት) ማቅረብ

·         ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 3 በሁለት ኮፒ መሙላት

·         የአገልግሎት ክፍያ፡-

o    200 US ዶላር በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም

5. የጠፋ ወይም የተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ስለመተካት

·         ለጠፋ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ምትክ ሊሰጠው የሚችለው መታወቂው ስለመጥፋቱ ከአካባቢው ፖሊስ ወይም አግባብ ካለው አካል በቂ የሆነ ማስረጃ ሲቀርብና የጠፋው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ዝርዝር ለኢሚግሬሽን ሲተላለፍ ነው

·         የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲተካ ጥያቄ ያቀረበው በመጀመሪያ መታወቂውን ከሰጠው አካል ውጭ ከሆነ ጥያቄው የቀረበለት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ወይም ኢሚግሬሽን የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ መጀመሪያ የሰጠውን አካል እንደአስፈላጊነቱ መረጃና በጥያቄው ላይ ያለውን አስተያየት መጠየቅ ይኖርበታል፡

·         ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅፅ 4 በሁለት ኮፒ መሙላት

·         አመልካች የአገልግሎት ክፍያ 200 የአሜሪካን ዶላር እና ለመጀመሪያ ጊዜ ምትክ ሲሰጥ በመደበኛ ክፍያ ላይ ተጨማሪ 50% በዕለቱ ምንዛሬ ወደ ዩሮ ተለውጦ ክፍያው  ሲፈፀም

·         አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ከመጠየቃቸው በፊትበቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው ቆንስላ ክፍል ይሰጣል

·         የትውልድ ኢትዮጵያ ለማደስ ወደ ኢምባሲው በአካል ቀርበው ለሚጠይቁገት አገልጋዮች በቅድሚያ በስልክ ቀጠሮ አስይዘው አሻራ በኤምባሲው በቆንስላ ክፍል ይሰጣል

የውክልና እና የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ

ውክልና መስጠት
የውክልና ሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት
እባክዎ አ ገልግሎቱን ለማግኘት መመሪያውን በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊዎቹን ማስረጃዎች ከነፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡፡
ሀ/ ዜግነትዎ ኢትያጵያዊ ከሆኑ ወይም  የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካለዎት

o    ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል ልከው ማስፈፀም የሚፈልጉ ውክልናውን በእንግሊዘኛና በሚኖሩበት አገር ኦፊሻል ቋንቋ አስተርጉመው ኖተራይዝ ካስደረጉ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማረጋገጥ ማቅረብ/መላክ ያስፈልጋል፡፡

o    ውክልናውን በፖስታ ቤት ተልኮ የሚፈፀም ከሆነ  የውክልና ሰነዱንና  አድራሻዎ የተጻፈበት የመመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ በማዘጋጀት አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

o    የመላኪያም ሆነ የመመለሻ ፖስታውን ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡

o    ጉዳይዎ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ከፈለጉ ኤምባሲው ከተረከበበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ፡፡

ለ/ የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ (አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው)

o    አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል በመላክ የሚያስፈጽሙ ከሆነ የመላኪያም ሆነ የመመለሻ ፖስታውን ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡

ውክልና የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት በተገልጋዮች መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

ሀ/ የአትዮጵያ ዜግነት ላላቸው

§  ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ (ሞዴሉን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ)

§   አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ

§   በሚኖሩበት አገር ያሉበትን ሁኔታ (status) የሚያሳይ ማስረጃ  ኮፒ

§  የመኖሪያ ፈቃድ  ወይም

§  የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የተሠጠ የቀጠሮ ወረቀት ወይም

§  ልዩ የመኖሪያ ፈቃድ

§  ወይምጊዜው ያላበቃ የመግቢያ ቪዛ

§   የአገልግሎት ክፍያ 57 ዩሮ  ሲሆን፣ ክፍያው ለኤምባሲው በተፃፈ

·         የሐዋላ ክፍያ  /MONDANT CASH/ ወይም

·          ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ መፈፀም ይቻላል፡፡

·         ውክልናውን በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያውን  በጥሬ ገንዘብ መፈፀም ይቻላል፡፡ ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ለ. የትውልደ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ለያዙ

·         ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ (ሞዴሉን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ)

·         የታደሰ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ

·         የአገልግሎት ክፍያ 57 ዩሮ  (በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው) ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ የሚኖርበት ሆኖ ክፍያው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በፓሪስ የተፃፈ

·          የሐዋላ ክፍያ /MONDANT CASH/ ወይም

·          ካሽየር ቼክ /Cashier Check/  መፈፀም ይቻላል፡፡

·         ውክልናውን በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያውን  በጥሬ ገንዘብ መፈፀም ይቻላል፡፡ ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ያስፈልጋል፡፡

ሐ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ  (አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም   በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው)

1.     አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት ኮፒ

2.     የአገልግሎት ክፍያ 87 ዩሮ  (በአካል ቀርበው የሚያስፈጽሙ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው በጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው) ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ  የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ የሚኖርበት ሆኖ ክፍያው ለኢትዮጵያ ለኤምባሲ በፓሪስ የተፃፈ

·         የክፍያ ትዕዛዝ  /MONDANT CASH/ ወይም

           ካሽየር ቼክ /Cashier Check/